30/01/2019
♨ተስፋህ በፈጣሪ ከሆነ አትወድቅም
♨በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ካጣኸው በኃላ ይቆጭሀል እና
♨ባጣኸው ነገር አትበሳጭ የተሻለውን ፈጣሪ ይሰጥሀል እና
♨የበደለህን ይቅር በል አምላክ ይቅር ባዮችን ይወዳል እና
♨ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ጌታህን አመስግን እርሱ አመስጋኞችን ይወዳል እና
🌈 ባለህ ነገር አመስግን ፈጣሪን ይጨምርልሀል እና
🌈በወንድምህ ውድቀት አትደሰት ነገ ሌላ ቀን ነው ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና
🌈የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ እርሱ ካንተ ጋር ነው እና
🌈ድሆችን እርዳ ሰደቃ/ምፅዋት ወንጀልን ታብሳለች እና
🌈ሰወችን አትመቃኝ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለች እና
🌈ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነው እና
🌈 አምላክህን አፍቅረው እሱ የእውነተኛ ፍቅር ባለቤት ነው እና
🌈 ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ ነው እና
🌈 ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም ውሳኔው የፈጣሪ ነው እና
🌈በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አምላክ ከታጋሾች ጋር ነው እና
🌈 ለሁሉም ነገር አትቸኩል ችኮላ የሸይጧን ነው እና
🌈 አትበሳጭ ብስጭት የሸይጧንን በር ትከፍታለች እና
🌈 የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ ያስታውስሀል እና።
እነኝህን ምክሮች ላይክ አና ሼር አድርግ ያወቁትን ማካፈል ጥበብ ነውና።
ፔጁን ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ