27/12/2020
ብርሃን ባንክ በገበያ ላይ ካሉት ባንኮች ዝቅተኛ ክፍያ እየፈፀመ እንዳለ ሁሉም ሰራተኞች ገለፁ፡፡ ከዚህም በተነሳ ሰራተኛው በከፍተኛ ሁኔታ ባንኩን እየለቀቀ እንዳለ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ባንኩ ለሰራተኛው ለወደ ፍት ምን መስራት እንዳቀደ የሚታይ ነገር ባለመኖሩ ሁሉም ሰራተኛ ባንኩ ላይ እምነት እያጣ መሆኑን አንዳንድ ዞረን ያነጋገርናቸው ሰራተኞች እየገለፁልን ነው፡፡ በአሁን ሰዓት ለቤት ክራይ 200/ሁለት መቶ ብር እና ለነዳጅ 30 ሊትር እየከፈለ የሚገኘው ብቸኛው ባንክ መሆኑም እጅግ ይገርማል፡፡