Etbitcoin

Etbitcoin Etbitcoin is an African Bitcoin mining firm. Etbitcoin offers Cryptohardware ans software solutions to anyone interested.

30/10/2019

Let us know how these articles are helping and don't forget to write feedbak ! Stay blessed!

30/10/2019

ቢትኮይን እና የመገበያያ ገንዘብ የወደፊት እጣ!!
ስለ ማንኛውም አይነት መገበያያ ገንዘብ የወደፊት እጣ ከማሳየታችን በፊት ያፕ የሚባሉ በ 1900 መጀመርያዎቹ በማይክሮኔዢያ ይኖሩ ስለነበረ የህብረተሰብ ባህል ታሪክ ጥቂት እናሳያችሁ:: ስለ ያፕ ልንነግራችሁ የፈለግንበት ምክንያት ይጠቀሙበት የነበረው የገንዘብ አይነት በጣም ስለሚገርም ነው:: እንደ ገንዘብ ይጠቀሙበት የነበረው ‘’ራይ’’ተብሎ የሚጠራ ላይም ተብሎ በሚታወቀው ድንጋይ የተሰራ ዲስክ ነበር በእርግጥ እንደኛ ገንዘብ አንቀሳቅሰው ተዘዋውረው ለመሸጥ እና ለመለወጥ አይችሉም ነበር :: ምክንያቱ ድንጋዩ እጅግ በጣም ትልቅ ስለነበረ ነው ከሁሉ ትልቅ የነበረው 3600 ኪሎ ግራም የሚመዝን እና 3.7 ሜትር ርዝመት ነበረው። የሚጠቀሙት መንገድ ደግሞ ማን የየትኛው ድንጋይ ክፍል ባለቤት እንደሆነ በመመዝገብ እና በመከታተል ነበር::
ከነዚህ ድንጋዮች አንዱን መስራት የቻለ ሰው በደሴቲቷ ላይ ሀይል እንዳለው ያሳያል:: “ያፕ” ይኖሩበት የነበረው ደሴት ላይም የተባለው ድንጋይ ስለሌለ ይህንን ከባድ የሆነ ድንጋይ ለማምጣት ወደ ሌላ ደሴት ጉዞ ማድረግ የግድ ነበር እንደውም ከድንጋዮቹ አንዱን በውቂያኖስ ላይ ሲያዘዋውር ከነበረ ጀልባ ላይ ድንጋዩ በወሀ ውስጥ ስለ መውደቁ የሚነገር ታሪክ ነበር
ተጓዦቹ ሲመለሱ የተፈጠረውን ነገር ለሁሉም ተናገሩ የተነገራቸውም እውነት እንደሆነ አመኑ ምንም እንኳን ድንጋዩ ከውቅያኖሱ በታች ቢሆንም እንዳለ ተቆጥሮ እንደመገበያያ ባባለቤትነት ይጠቀሙበት ነበር::
ስታስቡት ይህ አነስተኛ የማይክሮኔዢያ ባህል ከመቶ አመታት በፊት ብቻ ይጠቀሙበት የነበረ ይመስላችሁ ይሆናል ነገርግን የ “ያፕ” ህብረተሰብ እነዚህን ድንጋዮች እስከ አሁን ድረስ ይጠቀሙባቸዋል:: እንደዚህ አይነት ነገሮች በምእራቡ አለምም ይከሰታሉ በ1932 የፈረንሳይ ባንክ አሜሪካንን በዶላር ያላቸውን ነብረት እና ይዞታ ወደ ወርቅ እንዲቀይሩላቸው ተይቀው ነበር:: ነገር ግን በግዜው ወርቁን ወደ አውሮፓ ለመላክ አመቺ ሁኔታ ባለመፈጠሩ በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ወርቁ ወዳለበት ቦታ በመሄድ ወርቁን የፈረንሳይ ንብረት ብለው ሰየሙት በዚህም ፈረንሳይ የወርቁ ባለቤት እንደሆነች ተስማሙ:: በርግጥም ከ “ራይ” ድንጋዮች ጋር ተመሳሳይነት አለው:: ወርቁ ሳይንቀሳቀስ፣ በገሀዱአለም ምንም አይነት የሚታይ ለውጥ ሳይኖር
በመሰየም ብቻ በአሜሪካ ኢኮኖሚ ላይ ተጽእኖ በማሳደር፡ ያላቸው በራስ መተማመን እንዲቀንስ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል ይህም አሜሪካ ከወርቅ ተጠቃሚነት ዘወር እንድትል አድርጓታል::
በእነዚህ ሁሉት ምሳሌዎች ልናሳይ የፈለግነው ነገር በተፈጥሮው ድንጋይም፣ ሳንቲምም ሆነ የብር ኖት ምንም አይነት ተፈላጊነት ወይም ዋጋ ሊኖረው የሚያስችል ምክንያት የለውም ነገር ግን የሁላችን ስምምነት እነዚህ ነገሮች ዋጋ እንዲኖራቸው ያደርጋል ስለዚህም ኖራቸው:: ገንዘብ እርስ በእርሳችን ባለን ግንኙነት በምናካሂደው የመሸጥ እና የመለወጥ እንቅስቃሴ ማካሄጃ ነው:: ገንዘብ ቦታ የሚሰጠው ነገር አይደለም ነገርግን እኛ እርስ በእርሳችን ስለዋጋው እና ስለአስፈላጊነቱ የተነጋገርናቸው የፈጠራ ታሪኮች ቦታ እንድንሰጠው አድርጓል:: ይህ እጅግ በጣም የሚገርም ሀሳብ ነው::
አለማችን በሙሉ የተመረኮዘው በክፍያ ላይ ነው ገንዘብ ደግሞ መንገድ ጠራጊ ነው:: ገንዘብ ምግብ፣መብራት እና ሌሎች የሚያስፈልጉንን ነገሮች ለመግዛት እንጠቀምበታለን:: በተጨማሪም እርዳታ ለመስጠትም ሆነ ኢንቨስት ለማድረግ እንጠቀምበታለን:: ምን ማጥናት እንዳለብን እና ሰረተን ያጥራቀምነውን ገነዘብ በምን ላይ ማዋል እንዳለብን ምርጫው የኛ ነው::ነገርግን በዚህ የሚገባውን ክብር ባልሰጠነው አለም እነዚህ ነገሮች በተለያዩ መሰናክሎች ምክንያት በተመቻቸ መልኩ ሊሄዱ ስለማይቻላቸው በአጠቃቀምእና በምርት ላይ የተፈለገውን ያህል እድገት እንዳይመጣ ያደርጋሉ:: የማዘዋወርያ ነገሮችን የማስፈጸምያ ክፍያ ሁሌም አለ ::
ካለፉት ሁለት አስርት አመታት ጀምሮ ዲጂታል ገንዘብ መጠቀም ጀምረናል በቀጥታ ወደ ባንክ በማስገባት ክፍያ መቀበልም ሆነ መፈጸም ችለናል የቤት ክራይ መክፈል፣ በባንክ ክፍያ ካርድ ምግብ መግዛት እና ግብር መክፈል እና ከሚከፈለን የተወሰነው ደግሞ ተቆርጦ ለጡረታ ይገባል:: ይህ ሁሉ ነገር እንዲካሄድ የሚያደርገው በኮምፒውተር ላይ የአንድ እና የዜሮ መቀያየር ነው:: እንደ ሳንቲም ወይም እንደ ድንጋይ ምንም አይነት የሚጨበጥ ነገር እንኳን ሳናይ ይህ ሁሉ ነገር ይፈጸማል::
ዲጂታል ገንዘብ ነገሮችን ከማቃለሉ የተነሳ በሰከንዶች ውስጥ አንድ ካምፓኒ ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንችላለን ወይም በየትኛውም የአለማችን ክፍል ላለ ሰው ክፍያ መፈጸም እንችላለን::
ይሄ ሁሉ ነገር በተሳካ መልኩ የሚፈጸመው ታላላቅ ማዕከላት ዋስትና በመውሰድ እና በመስጠት በኮምፒውተር ላይ የሚቀያየሩትን እያንዳንዱን በአንድ እና በዜሮ የሚተላለፈውን መረጃ በመቀበል ነው:: በትክክል ካልተፈጸመ ደግሞ የእነዚህ ማዕከላት ስህተት ነው ወይም ደግሞ የተፈጠረውን ስህተት ማረም የነዚሁ ማዕከላት ድርሻ ይሆናል:: በስርአቱ ውስጥ ብዙ ፍትጊያ ስላለ አብዛኛውን ግዜ ግን ይሄንን ስህተታቸውን አያስተካክሉም:: ቺፕ እና ፒን ወይም ክሬዲት ወይም ዴቢት ካርድ በመጠቀም ለተጠቀሙት አገልግሎት ወይም ለፈጸሙት ግብይት በስሊፕ ላይ ከመፈረም ይልቅ የግል መለያ ቁጥር በማስገባት የሚካሄደወን የክፍያ መንገድ ለመተግበር የአሜሪካ ኩብንያዎች ምን ያህል ጊዜ ፈጀባቸው? ብዙ ጊዜ በምንጓዝበት ወቅት አብዛኛዎቹ ክሬዲት ካርዶች አይሰሩም ወይም ከመጠን ያለፈ ክፍያ ይጠይቃሉ ፍትጊያ የምንለው እንደዚ አይነት አሰራርን ነው:: በህንድ የሚኖር ስራ ፈጣሪ በኢንተርኔት የሚሰራ ስራ ቢፈጥር ብድር ለማግኘትም ሆነ ክፍያ ለመቀበል እጅግ በጣም ውድ ይሆንበታል::ፍትጊያ::
ዲጂታል ገንዘብ ለማግኘት ያለን መንገድ እና በነጻነት መለዋወጥ እንዳንችል በጌትኪፐሮች ወይም ጥበቃዎች የተገደበ ነው
የትም ብንሄድ፣ብንመለከት ይህንን እንቅስቃሴ የሚያጓትቱ እንቅፋቶች አሉ:: ምክንያቱም ዲጂታል ገንዘብ የኛ አይደለም ባባንካችን፣የኢንቨስትመንት ተቋም ወይም የክሪዲት ካርድ ኩባንያ ዳታ ቤዝ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኝ ነገርነው:: እነዚህ ተቋማት ይህን መዝገብ ይቆጣጠሩታል ስለዚህም ሊከለክሉን ይችላሉ:: የፔይፓል ነጋዴ ብንሆን እና የፔይፓል አልጎሪዝም በስህተት አጭበርባሪ ቢለን ያሉን አካውንቶች ታግደው ክፍያ መቀበል አንችልም ማለት ነው::
እነዚህ ማዕከላት ያልተሰራ ነገር ለመስራት ወይም አዲስ ሃሳብ ለመፍጠር መንገዶችን በመዝጋት የፈጠራ ስራዎች ተግባብተው እንዳይሰሩ ከባድ አድርገውታል :: ስንቶ ቻችን የፌስቡክ፣የጉግል፣የኢንስታግራም ፎቶዎቻችንን እንጠቀማለን ፎቶዎቻችን በየቦታው ተሰራጭተው ይገኛሉ:: በሙሉ በተለያዩ መገልገያዎች ይገኛሉ በካሜራችን ላይ፣በሀርድ ድራይቫችን ላይ፣በዌብ ሳይቶ ችላይ:: እነዚህ መገልገያዎች እርስበእርሳቸው ተግባብተው በህብረት አይሰሩም በዚህም ምክንያት የፎቶ ላይብረሪ ለማስተካከል ያስቸግራል የተደበላለቀ ነው:: እንዲሁ የተለያዩ ታላላቅ ማዕከላት የገንዘብ ማሰራጫውን ሲቆጣጠሩት ተመሳሳይ ችግር ያጋጥመናል የሚሰጡት አገልግሎትእርስ በእርስ ተግባብተው አይሰሩም ስለዚህም በክፍያ የምናካሂዳቸውን ነገሮች ይገድብብናል ስለዚህም የማዘዋወርያ ወይም የመላኪያ ክፍያዎችን ከፍ እንዲሉ ያደርጋል::
ሁለት የገንዘብ ደረጃዎችን አሳልፈናል
በአናሎጉ አለም በተወሰነ ፍጥነት በሰዎች ፍጥነት ነገሮ ችን በአካል አንቀሳቅሰናል:: በዲጂታል ዓለም ገንዘብበፍጥነት ይደርሳል ነገርግን በጌትኪፐሮቹ ወይም በጥበቃዎቹ ተቋማት መልካም ፍቃደኝነት ስር ወድቀናል ገንዘብ የሚንቀሳቀሰው በባንኮቹ ፍጥነት ብቻ ነው::
ወደ አዲሱ የገንዘብ ምዕራፍ እየገባን እንገኛለን ገንዘብ የወደፊት ዕጣው ፕሮግራም መደረግ ነው:: በገንዘብ ላይ ሶፍትዌር ሲጨመርበት ገንዘብ አንድየተወሰነ ዋጋ ያለውብቻ አይሆንም እናም ለጥበቃው በተቋማት ላይ ሀሳባችንን መጣል አይጠበቅብንም:: ፕሮግራም በሚደረግዓለም ውስጥ የሰው እና የተቋማትን እርዳታ ከሉፑ ውስጥ እናወጣለን:: ይህ ሲሆን እየተለዋወጥን እስከማይመስለን ድረስሶፍትዌሩ ገንዘቡን ወደ ተፈለገበት ያለምንም እንከን ይልክልናል::
የለውጡን የመጀመርያ እርምጃ የተራመዱት ክሪፕቶከረንሲዎች ናቸው:: ክሪፕቶከረንሲዎች ዲጂታል ገንዘብ ሲሆኑ በማንኛውም ባንክ ወይም መንግስት የማይተዳደሩ ናቸው:: ዲዛይን ሲደረጉም ያለምንም መሀከል ገቢ ገንዘብ በመላው ዓለም እንዲሰራ ለማድረግ ነው:: ቢትኮይን ከክሪፕቶከረንሲዎች እጅግ በጣም የገነነ ነው:: ኢቲሪየም፣ላይትኮይን፣ስቴላር እና ዶጅኮይን ደግም በጣም የታወቁ ናቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሌሎችም አሉ::
እናም እነዚህ እውነተኛ ገንዘቦች ናቸው አንዳንድ ምግብ ቤቶች ቢትኮይንን ይቀበላሉ:: ስልካችን ላይ በሚጫን አፕሊኬሽን ሌሎች ነገሮችን መግዛት እንችላለን:: ለትንንሽ ክፍያዎች ብቻ አይደለም ከዚህ በፊት 100,000 ቢትኮይኖችን ያንቀሳቀሰ ትራንዛክሽንተካሂዶ ነበር ይህም 40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያህልነው::
ይህ እንዴት ይሰራል? የሚለውን በሚቀጥለው እናያለን ...............follow us!!!
እናመሰግናለን!!!

ቢትኮይን ለመጀመርያ ግዜ ከ10,000 ዶላር በላይ ሆኗል። ይህም የሆነበት አንደኛው እና ዋነኛው ምክንያት  የ Chicago Mercantile Exchange ቢትኮይንን ወደፊት የመሸጥ የመለወጥ...
30/11/2017

ቢትኮይን ለመጀመርያ ግዜ ከ10,000 ዶላር በላይ ሆኗል። ይህም የሆነበት አንደኛው እና ዋነኛው ምክንያት የ Chicago Mercantile Exchange ቢትኮይንን ወደፊት የመሸጥ የመለወጥ አላማ እንዳላቸው ይፋ ካወጡ በኋላ ሲሆን ኢንቬስተሮች ይህ እድል እንዳያመልጣቸው ባደረጉት እንቅስቃሴ የአንድ ቢትኮይን ዋጋ ከ10,000 ዶላር በላይ እንዲያወጣ የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል።

በዚህ አድራሻ ተመዝግበው የቀረዉን አለም ይቀላቀሉ

HOME Get started with coin mining and generate your own coins. Minersale is an A-to-Z altcoin and Bitcoin cloud mining service Managed Cloud Mining Invest in an easy and fully managed altcoin and Bitcoin mining service and immediately start getting benefits without the need of being an expert in the...

14/11/2017

Dear Etbitcoin family
We are happy to let you know that registering on our mining pool is 100% free and it is the first step towards understanding Cryptocurrency. Register NOW!! And we will inform you when the legal issue is resolved. Fingers crossed!!

HOME Get started with coin mining and generate your own coins. Minersale is a bitcoin and alt coin mining solution from A to Z Managed Cloud Mining Invest in an easy and fully managed altcoin and Bitcoin mining service and immediately start getting benefits without the need of being an expert in the...

01/11/2017

Dear Etbitcoin Family
Because of the rules and regulations in Ethiopia, we are currently unable to find a way to make it work. We are a legitimate company based in London so we will operate legitimately and freely , for the sake of our clients. But we are still allowing people to register and wait until this issue is resolved.

28/10/2017

Dear Friends
We are offering a chance to everyone to try out our new mining pool !And encouraging everyone ,who is interested in investing to visit our hardware facility in london. We are using minersale hardware for mining Cryptocurrencies. we have the best percentage than any other mining pools. visit our pool at

HOME Get started with coin mining and generate your own coins. Minersale is a bitcoin and alt coin mining solution from A to Z Managed Mining Invest in coin managed mining and get all the benefits without getting deep in mining process. Pool Connect your miners to our mining pools. We charge only 0....

28/10/2017

when we say we have the best percentage on cryptocurrencies we don't just say we show , Follow us.

28/10/2017

When it comes to the world of investing, three words come to mind: overwhelming, intimidating, and scary. But We will be with you on every step you take with our Minersale mining pool.

10/10/2017

Amazing News For Ethiopian Diasporas, you now can invest in Bitcoin or any other Cryptocurrency. Expats living in Ethiopia are already involved with us.

Address

Etbitcoin
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Etbitcoin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share