Hosanna Bank ሆሳዕና ባንክ

Hosanna Bank ሆሳዕና ባንክ የባለሀገሩን የኢኮኖሚ ትንሣኤ አብሳሪ ባንክ።
Renaissance Bank For Rural Ethiopian Economy!!

ያልተዘመረላቸው የከምባታ ጠምባሮና የሀዲያ ጀግኖች በአድዋ (1888 ዓም) እና በማይጨው(1928 ዓም) ፀረ—ፋሺስት ኢጣልያ ጦርነቶችከአምባሳደር ተስፋዬ ሐቢሶ ሃይዴቦ እና አባገዳ መንገሻ ጎቤ...
31/12/2024

ያልተዘመረላቸው የከምባታ ጠምባሮና የሀዲያ ጀግኖች በአድዋ (1888 ዓም) እና በማይጨው(1928 ዓም)
ፀረ—ፋሺስት ኢጣልያ ጦርነቶች

ከአምባሳደር ተስፋዬ ሐቢሶ ሃይዴቦ እና አባገዳ መንገሻ ጎቤቦ አንጀጆ፣ 26/09/2012

"የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ያፈሰሱት ላብና ደም እስከዛሬ በተፃፉት የኢትዮጵያ ታሪክ ማስታወሻዎች ውስጥ ተመዝግቦ ባይገኝም የነዚህ ህዝቦች አስተዋፅኦ ባይታከልበት ኖሮ በ1888 የተገኘውን የአድዋ ድል ለመጎናፀፍ አይቻልም ነበር። ዳግማዊ አፄ ምኒልክም አፄአዊ ግዛታቸውን ለማስፋፋት የቻሉበት ታሪክ እውን ሊሆን ባልበቃም ነበር። ኢትዮጵያም በዘመናዊው የአለም ፖለቲካ መድረክ የተጫወተችውን ሚና እውን ለማድረግ ፈፅሞ የማይቻላት እንደነበር የታወቀ ከመሆኑም ባሻገር በአለምአቀፍ ደረጃ የአፍሪቃዊ ስልጣኔና መንግሥትነት አይነተኛ ምሳሌና ተምሳሌት ለመሆን ባልበቃችም ነበር።" (Wendy James, The Southern Marches of Imperial Ethiopia, 1986, p.xiv)

1.መግቢያ፣

ከላይ በተጠቀሰው ምንባብ በትክክል እንደተገለጸው፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ለኢትዮጵያ አንድነትና ህልውና ያበረከቱት አስተዋፅኦ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነበር-— የኦሮሞ፣ የሲዳማ፣ የሀዲያ፣ የጉራጌ፣ የከምባታ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የጎፋ፣ የጌዴኦ፣ የቡርጂ፣ የዳውሮ፣ የየም፣ የከፋ፣ የጠምባሮ እና የበርካታ ሌሎች የደቡብ ህዝቦች የሚጋሩት ታሪክ። ዛሬ የካቲት 23/2008 የአድዋን 120ኛ አመት የድል በአል በከፍተኛ ወኔና ስሜት በምናከብርበት ወቅት "ክርስቶስም ለወገኖቹ/ለስጋው አደላ" እንዲሉ እኛም የዚህ መጣጥፍ አዘጋጆች የራሳችን የስጋ ወገኖች የሆኑት የከምባታና የሐዲያ ሕዝቦች በ1888 አም በአድዋ፣ በ1928 ደግሞ በማይጨው ጦርነቶች ያበረከቱትን ተጋድሎ ባጭሩም ቢሆን ለማስታወስ ስለወደድን እነሆ—-፣

ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔረሰቦች አገር እንደመሆኗ ታሪኳ፣ ባህሏ፣ ሃይማኖቷ ሁሉ ህብረብሄር ገፅታ አለው። ዛሬ መንግሥታዊ ሉአላዊነቷ ሰፍኖ ያለበት የኢትዮጵያ ክልል ስፋትና ቅርፅ የሁሉም ብሔረሰቦች የደም፣ የህይወት፣ የጉልበትና የሀብት ድምር አስተዋጽኦ ያስገኘው ነው። ታሪካችን በትኩረትና በጥልቀት ቢመረመርና በሐቅ ቢፃፍ በአንድ ወይም በሁለት ብሔረሰቦች የተናጠል መስዋዕትነት የተሰራ ታሪክ በኢትዮጵያ እንደማይገኝ ልናረጋግጥ ይቻላል። በየዘመኑ ለአገሪቱ ነጻነት የፈሰሰው ደም፣ ወራሪን ለመከላከል የተደረገው ተጋድሎ፣ በየጦር ሜዳው የተመዘገበው ብሔራዊ ድል የአንድ ወይም የሁለት ብሔረሰቦች የትግል ግኝት ሳይሆን የብዙ ህዝቦች የደም፣ የህይወትና የመስዋዕትነት የጋራ ውጤት ነው። ባለፉት ዘመናት ተንሰራፍቶ በነበረው የስርአት በደልና ተፅእኖ ሳቢያ በርካታ ብሔረሰቦች የሚኖሩባት አገር ታሪክ የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ከቁጥር አስገብቶት አያውቅም፣ በዋሉበት የጦር ሜዳ ስማቸው ካለመጠራቱም በላይ በፈፀሙት ጀብዱ ሌላው ይጀግንበታል። መላው ብሔረሰቦች የተሳተፉበትንና ሕዝቦቻቸው ብርቱ መስዋዕትነት የከፈሉበትን ህብረብሄር ድል በጥቂት ብሔረሰቦች አባላት እንዲያውም በተወሰኑ ግለሰቦች ጀግንነት ብቻ የተገኘ አድርጐ በመመዝገቡና እውነትን በማዛባቱ በመላው ህዝቦች ዘንድ የታሪክነት አክብሮትን አጥቷል። ስለሆነም እያንዳንዱ ብሔረሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ሂደት ውስጥ የተሳተፈና ሙሉ የታሪክ ባለቤትነት መብት ያለው መሆኑን በማመንና በመቀበል የተማከለች ኢትዮጵያ ከተመሰረተች ወዲህ የአገሪቱን ዳርድንበር ለማስከበር በአድዋ(1888)፣ በማይጨውና በሌሎችም የጦርነት አውድማዎች የተፋለሙትንና የተሰውትን ጀግኖች ዝርዝር ዘግቦ ለታሪክ ማስታወሻነት ማቆየት የየብሄረሰቦቹ የታሪክ ምሁራን የቅድሚያ ሃላፊነትና ግዴታ ነው ብለን እናምናለን። ስለዚህም ነው ባለፉት ዘመናት በተለይም በአድዋና በማይጨው በወኔ የተሰለፉትንና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉትን የከምባታና የሀዲያ ተወላጆችን በቁንፅልም ቢሆን ለመዘከር የተነሳሳነው። በዚህ አጋጣሚ ለወገኖቻችን ምሁራን ለማሳሰብ የምንፈልገው ነገር ቢኖር የአድዋና የማይጨውን የክልሉን ዘማቾች በተመለከተ ከአዛውንት አባቶችና እናቶች እንዲሁም ከተለያዩ ምንጮች የሰበሰቡዋቸው መረጃዎች ካሉ በተቻለ ፍጥነት ቢልኩልን የተሟላ ታሪክ ለመፃፍ የሚያስችለን መሆኑን ነው።

2 የከምባታ ጠምባሮና የሀዲያ ዘማቾች በአድዋ ጦርነት(1888)

በአፄ ዳግማዊ ምኒልክ የጦር አበጋዞች የከምባታና የሀዲያን ክልል ህዝቦችን ለማስገበርና በማእከላዊ መንግሥት ስር ለማጠቃለል በ1882 አም የተጀመረው የጦርነት ዘመቻ የተጠናቀቀው በ1885 አም ላይ ሲሆን ከሶስት አመታት በሁዋላ በተቀሰቀሰው የአድዋ ጦርነት ላይ ገና ከቁስላቸው ያላገገሙት የክልሉ ህዝቦች ለአገራቸው ነፃነትና ሉአላዊነት ስሉ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ተዋግተዋል፣ ከፍተኛ መስዋዕትነትም ከፍለዋል። የአድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ በአፄ ዳግማዊ ምኒልክ የታወጀው በመስከረም ወር 1888 አም ነበር። የክተት አዋጁ እንደታወጀ የጎጃም፣ የቤጌምድር ፣የወሎና የላስታ ህዝብ ከ300 እስከ 500 ኪሎሜትር ያህል፣ የሸዋ፣ የሐረር ፣ የባሌ፣ የአርሲ፣ የከምባታና ሀዲያ፣ የሲዳሞ፣ የጅማ፣ የከፋ፣ የወላይታ፣ የወለጋና የኢሉባቡር ጦር ደግሞ ከ600 እስከ 1,000 ወይም 1,500 ኪሎሜትር ድረስ ርቀት ያለውን አገር በእግሩ እያቋረጠ ቀንና ሌሊት፣ ሃሩርና ቁር ሳይገታው አቀበቱንና ቁልቁለቱን እየወጣና እየወረደ ያለማወላወል ለወሳኙ ጦርነት ወደሰሜን የጦርነት ግንባር ተጓዘ።

የከምባታና የሐዲያ ክልል የነፍጠኛና የገባር ገበሬ ሠራዊትን በዋና የጦር አበጋዝነት የመሩት በ1888 አም የክልሉ ገዥ የነበሩት የአፄ ምኒልክ ያክስት ልጅ የነበሩት ደጃዝማች በሻህ አቦዬ ነበሩ። የከምባታን ዘማቾች የመሩት በወቅቱ የከምባታ ባላባት የነበሩት ቀኛዝማች ሞሊሶ ሄላሞ ድልበቶ ሲሆኑ ከእርሳቸው ጋር የዘመቱትን የከምባታ ገበሬ ጦረኞች የተሟላ ዝርዝር ለማግኘት ባንችልም 1) ላላምዳ መሎሮ፣ ከሄጎ ጌዮጣ፣ 2) አበጋዝ ትሮሬ ዋዶሌ፣ ከቃጫ፣3) ጌንቤራ ግዴቦ፣ ከደጋ ቀዲዳ፣ 4) ወልደማርያም ባጂ ፣ከገረምባ፤ 5/ መልከቶ ለታ ለቾሬ፣ ከሰረራ መዝመታቸውን የከምባታ አዛውንት አረጋግጠዋል። የሐዲያ ዘማቾች የተመሩት በፊታውራሪ ጌጃ ገርቦና በሌሎችም የሐዲያ መሪዎች እንደነበር ይነገራል፣ በጽሑፍ የተቀመጠ መረጃ ስለሌለን የዘማቾቹን ብዛትና የስም ዝርዝር ለማቅረብ አልተቻለም። በነበረው የዘመቻ ልማድ መሰረት ደጃዝማች በሻህ አቦዬ ወንድ ሴት ሳይባል በብዙ ሺህ የሚቆጠር የከምባታና የሀዲያን ገበሬ ሠራዊት ይዘው አድዋ ከደረሱ በሁዋላ ዳግማዊ ምኒልክ በሰጡዋቸው መመሪያ መሰረት ቀድመው የጠላትን ምሽግ የከበቡና ያስጨነቁ ጀግና ሰው እንደነበሩ ይተረካል።

የከምባታ ጦር በ1888 ዓም ከጣሊያን ወራሪ ጠላቶች ጋር በተደረገው የአድዋ ጦርነት የከምባታ ዘማቾች ስለፈጸሙት ጀብድና እንደኢትዮጵያን በአንድነትና በመተጋገዝ ተጋፍጠን በጋራ ስለተቀዳጀነው የአድዋ ድል...... ራሺያዊው ሰላይ Luwuandowisky , The History of Ancient Abyssinia በሚለው መፅሐፉና

-በምስራቅ አፍሪካ ፀረ -ጣሊያን ቡድን ያዘመተው እንግሊዛዊ ፀሐፊ Focler Henze The Victory of Black Community over Europe in Adwa ከገፅ 425 - 430 እንደዚህ ብሎ ይገልፃቸዋል።

- ለጉራና ለውሸት ድንፋታ ወይም ለሽለላ ከምባታዎች ብዙም ቦታ አይሰጡም ። በዘመናዊ ትጥቅ ታጅቦ የገባውን የጣሊያንን ጦር በፉከራና በቀረርቶ ማሸነፍ እንደማይቻል የተረዱት ከምባቶች ነበሩ ፣ የጠላትን ሀይል አቅጣጫ አስቶ በመግባት (ቆረጣ) ችሎታቸው ልዩ ነው። የስለላና የቆረጣ ውጊያ ለኢትዮጵያ ያስተዋወቁ ጀማሪዎችና መሐንዲሶች ፤ ብዙ ማውራት የማይፈልጉ እጅግ በጣም ጥበበኛ አርበኞች ናቸው ሲል ያሞካሻቸዋል።

- ከምባቶች የአድዋ ድል ባለውለታዎች ናቸው እንደእኔ እምነት የድሉ ቋሚ ሐውልት ናቸው ፣ ከምባቶች ያሳዩት አዲሱ የጦር ስልት ባይታከልበት ኖሮ የኢትዮጵያ አርበኞች በመንጋ እየሸለሉ ገብተው ያልቁ ነበር በማለት ይህንን እውነታ ይገልፀዋል።

ደጃዝማች በሻህ አቦዬ የከምባታና የሐዲያ ጀግኖችን አስከትለው በአድዋ የጦር ሜዳ በአምባ ኪዳነምህረት ግንባር ከኢጣሊያ የጦር አዛዥ ከጄኔራል አልቤርቶኒ ጦር ጋር በተደረገው ብርቱ ትንቅንቅ በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት ሲዋጉና ሲያዋጉ ሳለ በጠላት ጥይት ተመትተው የወደቁ ስመጥር የጦር ሰው ነበሩ። በመሪ አዝማቻቸው ሞት የተቆጩት ጭፍሮቻቸው ከጦርነቱ ፍፃሜ በሁዋላ ብዙ የኢጣልያ ምርኮኞችን ለአፄ ምኒልክ በማስረከብ ፈንታ በበቀል መፍጀታቸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል።

የአድዋ ጦርነትና የተገኘው አንፀባራቂ የኢትዮጵያውያን ድል መላውን አለም ያስደነቀ የታሪክ ክስተት ነበር፣ ለዝንተአለም የሚቆይ ታሪካዊ ድል። የአንዲቷ አፍሪቃዊት ነፃ አገር ኢትዮጵያ በኃይል ነፃነቷን ለመግፈፍ፣ ግዛቷን ለመድፈርና በሕዝቦቿ ላይ የተገዥነት ቀንበር ለመጫን ባህር ተሻግሮ የመጣን ጠላት የካቲት 23/1888 አም አድዋ ላይ ድባቅ መታች፣ ድል አደረገች። ከሁለት ሺህ አመታት በፊት ሀኒባል በሮማውያን ላይ ካገኘው ድል በማያንስ ሁኔታ በአለም ያስተጋባውና ኢጣልያኖችን ያሸማቀቀው የአድዋ ድል አፍሪቃ በአውሮጳ ላይ እንዳገኘው ድል የሚቆጠር ታላቅ የተጋድሎ ውጤት ነበር፣ ነውም። የአድዋ ድል የከምባታና የሐዲያ እንዲሁም የሌሎች ክልሎች ህዝቦች ሁሉ የአንድነት፣ የህብረትና የመስዋዕትነት ውጤት ከመሆኑም በላይ ማናቸውንም ተመሳሳይ ብሔራዊ ወይም አገርአቀፍ ችግርና ፈተና ለመቋቋምና በድል ለመወጣት የምንችለው እንደአድዋው ወቅት በህብረትና በአንድነት ስንቆም ብቻ እንደሆነ የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ድል ነው። በሌላ አንፃር ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውን ውድ ሕይወታቸውን የሰውበት ጦርነት ስለነበር ለበርካታ ሺህ ቤተሰቦች በመላ አገሪቱ የመሪር ሐዘን ወቀት እንደነበር መዘንጋት የለበትም። ሆኖም ለነፃነት የተከፈለ ውድ ዋጋ ነበር፣ ነፃነትም ምንኛ ውድ እሴት እንደሆነ ምንጊዜም መዘንጋት አይኖርብንም። አዎን፣ "ነፃነት ነፃ አይደለም"("Freedom is not free").

3 የከምባታ ጠምባሮና የሐዲያ ጀግኖች ሚና በማይጨው ጦርነት (1928)

የፋሺስት ኢጣልያ መንግሥት በ1888 በኢትዮጵያ ላይ የቅኝ አገዛዝ አላማውን ከግብ ለማድረስ ወረራ በከፈተበት ወቅት ኢትዮጵያውያን በአፄ ምኒልክ መሪነት ከዳር እስከዳር በአንድነት፣ በህብረትና በቆራጥነት ተነሳስተው ወደአድዋ የጦር ግንባር በመዝመት በወራሪው ላይ ያደረሱበት ሽንፈትና ሀፍረት ይታወሳል። ይህንን የበቀል ጦርነት ፋሺስት ኢጣልያ ከ40 አመታት በሁዋላ በ1928 አም በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነመንግስት በከፈተበት ወቅት ንጉሠነገሥቱ በዚሁ አመት መጀመሪያ ላይ ባስተላለፉት አገርአቀፍ ትእዛዝ መሠረት የየክልሎቹ ህዝቦች በየአገረገዝዎቹና በየአለቆቻቸው እየተሰለፉ ወደአዲስ አበባ እንዲገቡ ሲደረግ የከምባታ ጠምባሮና የሐዲያ ህዝቦችም 15,000 የገበሬና የነፍጠኛ ሠራዊት በመመልመል በዋና የጦር አዛዥ በደጃዝማች መሸሻ ወልዴ መሪነትና በቅርብ ረዳቶቻቸው በእነፊታውራሪ ታምራት ወልደሰማእትና ልጅ አበበ ወልደሰማእት (ሁለቱም ወንድማማቾች ከማይጨው ጦርነት በሁዋላ ወደከምባታ በመመለስ በአርበኝነት ወራሪ ጣልያኖችን ሲዋጉ ሳለ በዳውሮና በሻሸመኔ አካባቢ ተማርከው አሰቃቂ ሞት በጠላት እጅ እንዳጋጠማቸው ተረጋግጧል) እንዲሁም በከምባታና ሀዲያ ባላባቶችና አበጋዞች በመታገዝ በመስከረም ወር ወደአዲስ አበባ እንዲገቡ አድርገዋል። ከዚያም የሚያስፈልገው መሣሪያ እና ሌላም ቆሳቁስ እየተሰጣቸው ወደሰሜን፣ ደቡብና ምሥራቅ ወዘተ የጦር ግንባሮች እንዲዘምቱ ሲደረግ የከምባታና የሀዲያ ሠራዊት የዘመተው ወደሰሜን ግንባር ነበር። በዚህም መሰረት በመስከረም ወር 1928 አም ከአዲስ አበባ ተነስቶ ከ900 ኪሎሜትር በላይ የሆነ አስቸጋሪና ፈታኝ መንገድ በእግሩ እየተጓዘ ከአምስት ወሮች በሁዋላ የካቲት 8/1928 አም በትግራይ ጠቅላይ ግዛት በተንቤን አዉራጃ ወደሚገኘው የአቢአዲ ወረዳ ገብቶ የፃሂን ወንዝ በመመሸግ ለጦርነት ተዘጋጀ። ከዚያም በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት ከፃሂ ወንዝ ምሽግ ተንቀሳቅሰው የጠላት አውሮፕላኖች ከሰማይ፣ መትረየሶች፣ መድፎችና ታንኮች ከመሬት የመርዝ ቦምብና የጥይት አረር እያርከፈከፉባቸው በከፍተኛ ወኔና ጀግንነት ተዋግተውና አያሌ ጀግኖችን ሰዉተው በተንቤን የጦር ግንባር በኢጣልያ ወራሪ ሠራዊት የተከበቡትን የራስ ካሳ ኃይሉንና የራስ ስዩም መንገሻን ሠራዊት ከከበባው ቀለበት("ከብረት አጥር") ሰብረው እንዲወጡና ነፃ ለማስለቀቅ እንደበቁና ከፍተኛ አድናቆትን እንዳተረፉ ታሪክ ይመሰክራል ("የሃበሻ ጀብዱ"፣ ኮሎኔል አዶልፍ ፓርለሳክ፣ ቼኮዝሎቫኪያ፣ 1940፣ ገጽ 248—261)። ከዚያም ከተንቤን የፃሂ ወንዝ ተንቀሳቅሰው እስከጊባ ወንዝና እስከአሸንጌ ሃይቅ በተካሄደው ከባድ ጦርነት የሌሊት ቁር፣ የቀን ሀሩር፣ የውሃ ጥማት፣ የስንቅ እጥረትና ከሁሉም በላይ ከሰማይ የሚዘንብባቸውን የመርዝ ቦምብ ጢስ ተቋቋመው ለአገራቸው የማይዘነጋ መስዋዕትነት ከፍለዋል፣ አያሌ ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን በጦር ግንባሩ ለመገበር ተገድደዋል። ይህንን የታሪክ ማስታወሻ በጥንቃቄ ዘግቦና በ1940 አም በቼኮዝሎቫኪያ አገር አሳትሞልን የሄደው ኮሎኔል አዶልፍ ፓርለሳክ የቼኮዝሎቫኪያ ተወላጅ ሲሆን በወቅቱ የአጼ ኃይለሥላሴ መንግስት የጦር አማካሪና የጦርነቱ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ነበር፣ እርሱም ከመጀመሪያው አንስቶ የጦርነቱን አጀማመርና አካሄድ በእለት ማስታወሻዎች እየመዘገበ እስከጦርነቱ ፍጻሜ ድረስ ይከታተል የነበረ ወታደር ስለነበር ስለከምባታና ሀዲያ ተወላጆች የተለየ ጀግንነት የገለፀው ምስክርነት እጅግ የሚያኮራ ነበር። ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ውስጥ እንዲህ ሲል ነበር የገለፀው፣

1) " የካቲት 8 ቀን ማምሻው ላይ በጦር ሜዳ ጀግንነታቸው ወደር የሌላቸውና የማይገኝላቸው ወደ15,000 ገደማ የሚሆኑት የከምባታ ተወላጆች በጀግናው መሪያቸው በደጃዝማች መሸሻ ወልዴ እየተመሩ ከ900 ኪሎሜትር በላይ በእግራቸው ተጉዘው አቢአዲ ገቡ" (ገፅ 248)፣

2)" በዚህች ቀን ምሽት ደጃዝማች መንገሻ ሂልሚና ደከመኝን ከማያውቁት የከምባታ ልጆች ጋር በዚያው ምሽት እስካሁን በልጁ (አቢቹ) ጦር ብቻ ሲጠበቅ የነበረውን ቦታ በስተሰሜን በደብረአምባ በኩል የፃሂን የወንዝ ዳርቻ ይዘው መሸጉ " (ገፅ 248)፣

3) "በዚህ መልኩ እኛ ስንሸሽ ደጃዝማች መሸሻ የከምባታ ጦር አዝማች የራስ ካሳን ጦር የቀኝ ክንፍ በታላቅ ጀግንነት ሲከላከል የግራውን ክንፍ ሽፍቶችና ባንዳዎች አሰፍስፈው ሊወጉት የሚጠብቁትን የአቢቹ ጦር እየተከላከለ ጦሩ መስመር ይዞ ከተከበበበት የብረት አጥር ሰብሮ ወጣ" (ገፅ 260)።

ነገር ግን ቀጥሎ በተደረጉት ጦርነቶች ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ ከጣሊያን ወታደሮች በተወረወረባቸው የእጅ ቦምብና በመድፍ ጥይቶች ተመትተው የህይወታቸው መጨረሻ ሆነ። ከመሸሻ ሞት በሁዋላ የከምባታ ጦር በራስ ጌታቸው አባተ እዝ ስር ሆኖ ከጣልያን ወታደሮች ጋር የሞት የሽረት ፍልሚያ ቢያካሂዱም እንደተቀሩት የኢትዮጵያ ዘማቾች ሁሉ የሽንፈት መራራ ፅዋ ከመጎንጨት ለመዳን ባለመቻላቸው ወደመጡበት የከምባታ አውራጃ ግዛት ለመመለስ ከአካባቢው ሽፍቶችና ባንዳዎች የሚገጥማቸውን የደፈጣ ጥቃት እየተጋፈጡ ብዙ ወሮችን የፈጀ የ900 ኪሎሜትር አስቸጋሪና ፈታኝ የመልስ ጉዞ ተበታትነው ለመጉዋዝ ተገደዱ። ያ ሁሉ መስዋዕትነት ከኢጣልያኖች አውሮፕላኖች በሚዘንበው የመርዝ ቦምብ፣ የሠራዊት፣ የዘመናዊ መሣሪያና የታንክ የበላይነት የተነሣ ውጤት—አልባ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በውጭ ሃይሎች በተቃጣ ወረራ ሽንፈትን ለመከናነብ ተገደዱ። አዎን፣በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎችና ተግዳሮቶች ምክንያት የማይጨው ጦርነት በኢትዮጵያውያን ሽንፈት በመጠናቀቁ በየግንባሩ የተሰለፉት ሁሉ ወደየመጡባቸው ክልሎች አፈግፍገው አገራችን ነፃነቷን በ1933 አም እንደገና እስክትቀዳጅ ድረስ በአርበኝነት፣ አንዳንዶቹ በውስጥ አርበኝነት ለመዋጋት ተገድደዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የከምባታ ጠምባሮና የሐዲያ ተወላጅ ዘማቾች ወደየአካባቢያቸው በማፈግፈግ እንዳሉ "የነፍጠኞች መንግሥት ተሸንፎ በሽሽት ላይ ነው"፣ የሚል ወሬ እንደተሰማ የከምባታና ሀዲያ ህዝብ ከአፄ ምኒልክ ዘመነመንግስት ጀምሮ እስከማይጨው ዘመቻ ድረስ(1928 አም) ለ40 አመታት የደረሰበትን ግፍና በደል ለመበቀል በማሰብ የነፍጠኞች ከተማ የነበረውን የሆሳዕናን ማእከል ወርሮ በማቃጠሉና ብዙዎች የነፍጠኛ ቤተሰቦችና የከተማዋን ጠባቂዎች በመግደሉ የእነፊታውራሪ ታምራት ወልደሰማእትና ልጅ አበበ ወልደሰማእት ሠራዊት ወደሆሳእና ከደረሰ በሁዋላ የከምባታ አውራጃ ግዛት አጎራባች አውራጃዎች የነበሩትን ሁሉ በሁሉም አቅጣጫዎች በማስተባበር የሰነዘሩት የቂምበቀል የጅምላ ጭፍጨፋ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የከምባታና የሐዲያ ተወላጆችን እንደፈጀ አባቶች በቁጭት ዛሬም የሚያስታውሱት የታሪክ ጠባሳ ነው። በወቅቱ ወደማይጨው ግንባር የዘመቱት ጀግኖች ቤተሰቦች ሳይለዩ ሁሉም በጅምላ ከዳር እስከዳር በወላይታ፣ በጋሙጎፋ፣ በሁልባራግ፣ በስልጤ፣ በእነሞር፣ ወዘተ ወራሪ ሰራዊት በመፍጨፍጨፉ፣ በመሰለቡ፣ በባሪያነት ተፈንግሎ በመሸጡ ወዘተ በአውራጃው ህዝብ ዘንድ "ቄጊ በሪሃ" ("የደም ዘመን") ተብሎ ዛሬም ይታወሣል። የአውራጃው ዘማቾች ያንን ሁሉ የጦር ግንባር መከራና የፋሺስት ኢጣሊያን የቦምብ ዝናብ ተቋቋመሙና ምንም ፈተና ሳይበግራቸው ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ የጠበቃቸው የጀግኖች አቀባበል ሳይሆን ሚስቶቻቸው፣ ልጆቻቸው፣ ወላጆቻቸው፣ ዘመዶቻቸው ወዘተ ወይ ተገድለው፣ ተሰልበው ወይንም በባርነት ተሸጠው፣ ቤቶቻቸው ተቃጥለው፣ ንብረቶች ተዘርፈው እንዲሁም አያሌ ወገኖች ወደተለያዩ ክልሎች ተሰድደው ስለነበረ ምንጊዜም የማይዘነጋ የግፍ ግፍ፣ ድርብ ድርብርብ የሀዘንና የዋይታ ወቅት ነበር። "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ ንጉሠ ነገሥቱ ከስደት በ1933 አም ሲመለሱ የአውራጃውን የከምባታና የሐዲያ ህዝቦች እንደከዳተኛ ህዝቦች በመፈረጅ ቀደም ሲል በአርባ አመታት የነፍጠኛ አገዛዝ ዘመን ከተዘረፉት የመሬት ይዞታ የተረፈውን ቁርጥራጭ መሬት ሁሉ በመንጠቅ ለነፍጠኞች እንዲከፋፈል አደረጉ። የወጋ ቢረሳ፣ የተወጋ አይረሳምና ይህ ዘመን በከምባታና በሀዲያ ህዝቦች ዘንድ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባውም። ይህ ታሪካችን ሊረሳ ባይገባውም በኢትዮጵያ ደረጃ ዛሬም ሆነ ነገ ለሚኖረን ሰላማዊ አብሮነት (peaceful coexistence) ስንል ያንን የግፍ ታሪክ ይቅር በማለት ከሰሜን እስከደቡብ፣ ከምስራቅ እስከምእራብ፣ ከመሓል እስከዳር አገር ከሚኖሩ ከሁሉም ወገኖቻችን ጋር በወንድማማችነት ለመኖርና የቀድሞ ክፉ ታሪክ ዳግመኛ እንዳይከሰት በጋራ ከመታገል ውጭ ባንዳንድ የአገራችን ብሄረሰቦች ዘንድ አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም ሲል የሚታየውንና ወደዃላ የሚጎትተንን አፍራሽ አማራጭ ምንጊዜም ልናስብና ልናሰላስል አይገባንም፣ በፍፁም!!

ለማንኛውም፣ የታሪክ ማስታወሻ ሆኖ የዛሬዎቹን የከምባታ ጠምባሮና የሐዲያ ተወላጆች ያገለግል ዘንድ በማይጨው ጦርነት ወቅት ወደሰሜን የጦር ግንባር የዘመቱትን የክልሉን ዘማቾች ዝርዝር ለናሙና ያህል (ከወገኖቻችን የተሰጠንን መረጃ በመመርኮዝ) ከዚህ ቀጥሎ እናቀርባለን፣

ሀ/ ከከምባታ ጠምባሮ ብሔረሰቦች፣

1) ፊታውራሪ በርገኖ ሞሊሶ ሄላሞ(ባላባት)**

2) ቀኛዝማች ጩፋሞ ኦምቦሌ፣

3) ቀኛዝማች ሻንቆ ላጊሶ

4) ቀኛዝማች ማሞ ኤሽቼ፣

5)ግራዝማች መሀሩ ወልደማርያም፣

6) ግራዝማች መንቶሴ አጋጎ፣

7)ባላምባራስ ሲኮሬ ሃጃኖ፣

8) ባላምባራስ ተሎሬ ቤሌሎ፣

9) ባላምባራስ ቃሬቦ ሄላሞ ቡላዶ፣

10) ባላምባራስ ኦምበጎ ባራሞ፣

11) ዳኛ ሃንፉጮ ሴንደኖ

12) አቶ ጎበና ባሶሬ(በተንቤን ግንባር የተሰው)፣

13 አቶ ዋኖሬ ጊቼ( " "")፣

14) አቶ ጃሌ ኤሌሞ፣

15) አቶ ቢቢሶ ሉጌ

16) ዳኛ ኮያሞ ኦርታቦ፣

17) አቶ ዲጌቦ አቢቼ፣

18) አቶ ዳለሎ ወጫሶ

19 ወ/ሮ ጌጤ ኤርገና/የጀግና ሜዳልያና ጋሻ መሬት የተሸለሙ)

20) "ቀርቾ "/እመቤት ሰረቴ ጎንቼ/የፊታ በርገኖ ሞሊሶ ሚስት)፣

21) አቶ ኤጃሞ ማዴቦ፣

22) አቶ ኃይለማርያም ኤሽቼ

23) አቶ ኤርገና(ሃይለጊዮርጊስ) ሳዳሞ

24) አቶ ቦሎጬ(ዮሴፍ) ኤረንጎ

25) ዳኛ ሉጎ ለቴቦ (የተሰው)

26) ዳኛ ወልዴ ሌጋሞ(የተሰው)

27) ዳኛ ለፌቦ ባላሞ(የተሰው)

28) አቶ ሻሞ (ቆስለው የተመለሱ)

29) አቶ ደምሴ ወልደማርያም(የ5 አመቱ አርበኛ)፣

30) አቶ አዳል መልከቶ

31) አቶ ዳለቻ ሌጋሞ(የ5 አመቱ አርበኛ)

32) አቶ ደገሎ ጉንቱራ፣

33) አቶ ሜጤቦ አንጀጆ፣

34) አቶ ህሪጎ ጤአንሶ/ከሸሎ/

35) አቶ ላምቦሮ ጮራሞ፣

36) ዳኛ አበበ/ከጌዮጣ/፣

37) ዳኛ ሄራሞ/ከጠዛ/

38) አቶ ዋቸሞ ሰእልአሎ ጎቤቦ

39) አቶ ላንብዬ/ላምቦሮ/ እጃጆ

40) ወ/ሮ አመተማርያም መላና

41) አቶ ጎቴ ኤዳሞ/ቆስለው የተመለሱ /

42) ዳኛ ማሞሮ ላቴቦ

43) "ቦያና " ቦቤቶ ዋኖሬ/የተሰው /

44) ሾቢሶ ሃንቄቦ ኩማሎ /የተሰው/

45) አቶ ሞላ ኦቶሬ፣ 46) አቶ አዲሴ ለጫሞ፣

47) አቶ አቤ ጤአንሶ

48) አቶ በየነ ዋኖሬ፣

49) ወልደማርያም ሌጋሞ፣

50) ዳለሎ ትሮሬ፣

51) ዳለሎ ወጫሶ፣

52) ዱጌቦ አቢቼ፣

53) ገብሬ አንጀጆ፣

54) ጊዶሌ እልትሮ

55) ዋቸሞ ሰል‘አሎ ጎቤቦ፣

56) ዋኖሬ ጊቼ፣

57) ምሮቼ ገንባሌ፣

58) ማሞ ቶሄቦ

59) ቦጋለ ገጀሞ፣

60) ሄራሞ ጫክሶ

61) ላምቦሬ ቀልቦሬ፣

62) ሻሜቦ ባዴቦ

63) ሾቢሶ ኤጁቴ፣

64) ቢሆን ብጃሞ

65) አሹሮ እጃጆ፣

66) አንሼቦ ቦዬ

67) አባይ ኤራጎ፣

68) አኑሎ ማዴቦ

69) ኡሳሞ ኦልቦ፣

70) ኤርዱሎ በየነ

71) ኤጃሞ ማዴቦ፣

72) ወልዴ ድንቦሬ

73) ዋንጎሬ ጃንፋ፣

74) ግርሚሶ በጅጎ

75) ደንበሎ፣

76) ወልዴ ባዬ፣

77) አኑሎ ማዴቦ፣

78) ዋዴ አጭሶ፣

79) ዳኛ አኑሎ ማዴቦ፣

80) ኩማሎ አርጆ፣

81) ኤርሱሎ ዴዳንጎ፣

82) ሀብተማርያም ኦርዶሎ፣

83) ሄልሰቦ ኦንኬ ሱምቡሎ(አንድ አይናቸውን አጥተው የተመለሱ ጀግና)

84/ ቴራሶ (ሃይለሚካኤል) ቦያሞ
85/ ለፌቦ ዶንጌ (በተንቤን ግንባር በቦንብ ተመትተውና አንድ ዓይናቸውን አጥተው የተመለሱ ጀግና።

ከጠምባሮ ማህረሰብ መካከል የዘመቱት የሚከተሉት ናቸው፣

——————————————————

84) አቶ ደማኮ አኮ (የጠምባሮ ባላባት)፣★★

85) " ሳቆሬ ደነቦ፣

86) "ሊባቦ አጥሶ፣

87) ዳኛ ዶፌ ዴጣሞ፣

88) ዳኛ አየሞ አቢሎ፣

89) አቶ ዶዳ አኮ፣

90) " ከምበላ አኮ፣

91) " ባቦሬ ዶላሞ፣

92) "ሎራቶ ዳዎሬ፣

93) " ፈቶ ሳዴቦ፣

94) " ቦታራ በላኮ፣

95) " ሀይበሎ ሀዳሎ፣

96)" ሀንዲሶ ሃይበሎ፣

97) " መኖሬ አንደራ፣

98) "አበበ ማንዶዬ፣

99) " ያዬ ባላንጎ፣

100) " ሰብሮ አሳንቻ፣

101) " ሰመረ ላዕሶ፣

102) " በየነ ሱማሞ፣

103) " መኬቦ ሻሜቦ፣

104) " ቢረጋ ጌምቤራ፣

105) " ሜጊሶ ዋዴቦ፣

106) " ባራሞ ባላንጎ፣

107) " ብብሶ ደጊሶ፣

108) " አጊቼ ላዕሶ፣

109) ወ/ሮ ደለማ ካንዶ፣

110) አቶ አበቦ ናጬ፣

111) " በለዶ አታሮ፣

112) " ሃዳሮ ጮራሞ፣

113) " ላሞሬ ኡጌቦ፣

114) " አርፍጮ ሉዳጎ፣

115) " ደፈጫ ጮፎሮ፣

116) " ማንዶዬ ሳጌቶ፣

117) " አበበ ማንዶዬ፣

118) " ሀምቡሎ አዋኖ፣

119) " አኮ ሸለሞ፣

120) " ወንድሙ ባየህ፣

121) " ሃደሮ ኮንዴ፣

122) " አለሙ አጥሶ፣

123) " በሬዶ በሞ፣

124) " ቡልቂ በሻህ፣

125) " ጭነሾ ቀልቦሬ፣

126) " ሳዴቦ ዴቢሶ፣

127) " ገነሞ ግንታሞ፣

128) " አጣሞ ህብሶ (በጦርነቱ የተሰው)

129)" ደዋራ ሰርጦ " " " " " """""""""""""

130) " ለእሶ አታሮ፣ " """"""""""""""""""

131) " ሻሜቦ ዳንጎሬ፣ """"""""""""""""""""

132) " አኮ ሸለሞ፣ """""""""""""""""""""""""

133) " ዶላሞ ባቦሬ፣""""""""""""""""""""""""

134) " ህሪጎ አጣሞ፣ ”""""""""""""""""""""""

135) " ሃፌቦ አጣሞ፣ """""""""""""""""""""""

136) " ህርቦሮ አጣሞ፣ """"""""""""""""""""

137) " ሃዪቦ አጣሞ፣ """""""""""""""""""""

138) " ሊባቦ ባላንጎ፣ """""""""""""""""""""

139) " ባላንጎ ሰዴ፣ """"""""""""""""""""""""

140) " ናኔ ሞጆሮ፣ """""""""""""""""""""""""

ለ/ከሀዲያ ብሔረሰብ/ሻድገር እንደገኝ፣

1) ፊታውራሪ ጌጃ ገርቦ /የአድዋና የማይጨው ጀግና፣ በተንቤን ግንባር በአውሮፕላን ቦምብ ተቃጥለው የተሰው፣ በስማቸው "ጌጃ ሰፈር" በአዲስ አበባ የተሰየመላቸው/፣

2) ፊታውራሪ ገረዴ ጃባሞ፣
3) ፊታውራሪ ሺራጎ ሄመቾ

4) ቀኛዝማች ጢቀሞ ዱጉኖ፣

5) ቀኛዝማች ገብሬ ሱዱቦ/የተሰው ጀግና/፣
6) ቀኛዝማች ህርቦሮ አማዶ፣

7) ቀኛዝማች ወራቆ አጋጎ፣
8) ግራዝማች ዳድቼ ቄፈዶ፣
9) ግራዝማች ሎጵሶ አቢዮ

10) ግራዝማች ሃካንሶ ድጋዶ /የተሰው ጀግና/

11) ዳኛ ላምቤቦ ወራቆ/በርካታ የጣልያን ወታደሮችን በተንቤን የጦር ግንባር ከፈጁ በሁዋላ በአውሮፕላን ቦምብ ተቃጥለው የተሰው ጀግና/

12) ባሻ ወንድማገኝ ኡልገሶ/የላቀ ጀብዱ የፈፀሙ ጀግና/፣

13) አቶ ጌዲቾ ሄመቾ/የተሰው አርበኛ /

14) አቶ ኤርሲዶ ሄመቾ/የተሰው ጀግና/

15) አቶ ማሞ አኖሬ፣
16) ዳኛ ሹረሞ ላንገና፣
17) አቶ ሀብተማርያም ሶራሞ /ከሻሾጎ/

18) ባላምባራስ ላጊሶ፣ 19) አቶ አበበ ጎዴቦ፣
20) ግራዝማች ገነሞ ህርቦሮ

21) ባላምባራስ በሪሶ ህርቦሮ፣

22) አበጋዝ ጡንሴ ሜንሳሞ/ከራስ አበበ አረጋይ አርበኞች ጋር ተሰልፈው ለ5ት አመታት በአርበኝነት የተዋደቁ ጀግና/

23) አቶ ላምቤቦ ፉንዱሴ፣
24) አቶ አቡዬ/ከዳኔኦሬ ጎሳ/፣
25) አቶ ላምቦሬ ሀከንሶ/የተሰው/፣
26) አቶ አጢሶ ወጣኖ

26) አቶ ዲመንሶ ኤቤሮ፣
27) አቶ ኦርጅኖ ጫእሎ፣
28) አቶ ኦቾቾ ሉደጎ

የመረጃ ምንጮች

★★★★★*★*★

አቶ ኡታሎ ኤጁቴ ኩማሎ ዋቆ፣ አቶ ወጫቶ ላዕሶ፣ አቶ ወጫቶ ሎራቶ፣ የተከበሩ ተክሌ ተሰማ፣ "ገራድ" ወልደጊዮርጊስ ለጄቦ፣ አቶ ኃይሌ ማጊቾ፣ አባገዳ መንገሻ ጎቤቦ፣ አቶ አለሙ ጎቤቦ፣ አቶ ከበደ ሙጎሮ፣ አምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ፣ አቶ ማቴዎስ ማሞ

——————————————————

** ፊታውራሪ በርገኖ ሞሊሶ በተንቤን ግንባር ውጊያ ቆስለው ስለነበር ከሽንፈት መልስ ወደጎንደር ከተማ በመግባት ከአንድ አመት ቆይታ በሁዋላ ወደከምባታ ተመልሰው የባላባት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ቆይተው የካቲት 17/1937 አም በሞት ተለይተዋል፣ ለሞት ያበቃቸውም የጦር ሜዳ ቁስላቸው አመርቅዞ እንደነበር ከከምባታ አዛውንት ለመገንዘብችለናል። ከፊታ/በርገኖ ሞሊሶ ጋር በጎንደር የቆዩት1ኛ/ ባለቤታቸው እመት ሰረቴ ጎንቼ፣ 2ኛ/ ባላ/ሲኮሬ ሃጃኖ ከባለቤታቸው ከወ/ሮ አዳነች ወንዳየን እና 3ኛ/ አቶ አዲሴ ለጫሞ ነበሩ።

-**************-**************************-**

ደጃዝማች መሸሻ ወልዴ አሻግሬ፣ በ1928 ዓም የፀረ—ኢጣልያ ጦርነት ወቅት የከምባታና ሀዲያ የነፍጠኞችና የአርሶአደሮች ሠራዊት በግንባርቀደምነት የመሩና የተሰው ደፋር ጀግና ።

ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አረፉ   | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸ...
17/09/2024

ኘሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ አረፉ

| ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ፤ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስሰማ ከልብ አዝኛለሁ ብለዋል።

በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ ሲሉም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ያቆዩት ውርስ እና ቅርስ ፀንቶ እንዲቀጥል ነፍሳቸውም በሰላም እንድታርፍ ተመኝተዋል።

ማርቆስ 16¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁵ ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።⁶ እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ...
02/05/2021

ማርቆስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።
⁶ እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።
⁷ ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ለጴጥሮስም፦ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው።

ሆሳዕና በአርያም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ። “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” ማቴዎስ ...
25/04/2021

ሆሳዕና በአርያም በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነዉ። “የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም፦ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” ማቴዎስ 21፥9

ከፍተኛ ግብዓት የተገኘበት የምክክር እና የአክሲዮን ሽያጭ መድረክ
05/11/2020

ከፍተኛ ግብዓት የተገኘበት የምክክር እና የአክሲዮን ሽያጭ መድረክ

የአክሲዮን ሽያጭ ምሽት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል
05/11/2020

የአክሲዮን ሽያጭ ምሽት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል

31/10/2020

ሆሳዕና ባንክ የለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያውያን ባንክ !

29/10/2020
19/10/2020

አክሲዮኑን በሁሉም ባንኮች መላ ቅርንጫፎች እየተሸጠ ይገኛል።

22/09/2020

እንኳን ለያሆዴ: ለመስቀላ: ለጊፋታ ....ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!!
ለአዲስ ዘመን አዲስ ስጦታ ከሆሳዕና ባንክ
አክሲዮን ይግዙ ዘመኖን ያድሱ ።

Address

Africa Avenue , Bole , Genet Building 1st Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:30
Tuesday 09:00 - 17:30
Wednesday 09:00 - 17:30
Thursday 09:00 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Telephone

+251968099621

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hosanna Bank ሆሳዕና ባንክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hosanna Bank ሆሳዕና ባንክ:

Share

Category