Ethio Sacco

Ethio Sacco Ethiosacco | ኢትዮሳኮ ለገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ይሆናሉ የምንላቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፣ መረጃ ማድረሻ ፣ ትምህርት መስጫ የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ነው! The future is collective.

The future is green. The future is cooperative. Working Together For Better and Healthy Economic Development

 |ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሊጀምር መሆኑ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ይታደጋል ተባለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን በቀጥታ ለመቆጣ...
28/05/2026

|ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት ላይ ቀጥተኛ ቁጥጥር ሊጀምር መሆኑ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ይታደጋል ተባለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቁጠባና ብድር ማኅበራትን በቀጥታ ለመቆጣጠር የወሰነው እርምጃ፣ ዘርፉ ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መሸሸጊያ እንዳይሆን ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የፋይናንስ ባለሙያ ገለጹ።

ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ፤ ማኅበራቱ ከብሔራዊ ባንክ ቁጥጥር ውጪ መቆየታቸው በፋይናንስ ገበያው ላይ ከፍተኛ መዛባትና የደህንነት ስጋት ደቅነው መቆየታቸውን ለጣቢያችን ጠቁመዋል።

የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ እንደገለጹት፤ እስካሁን ማኅበራቱ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውስጥ አለመኖራቸው ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወይም "መኒ ላውንድሪንግ"ሰፊ በር ከፍቶ ቆይቷል።

ሕገ-ወጥ ገንዘብ ያላቸው አካላት የገንዘቡን ምንጭ ለመደበቅ በአባላት ቁጠባ ስም በትናንሹ እየከፋፈሉ ወደ ማኅበራቱ በማስገባት፣ ወደ ሕጋዊ የባንክ ሥርዓት እንዲቀላቀል ሲያደርጉት መቆየታቸውን ባለሙያው ጠቁመዋል።

አዲሱ አሰራር ግን ይህንን የገንዘብ ማጠብ ሥራ ለመቆጣጠር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።

ባለሙያው አክለውም፣ ማኅበራቱ እንደ ባንኮች ጥብቅ የካፒታልና የሥራ ማስኬጃ መመሪያዎች የማይገዟቸው መሆኑ በገበያው ላይ ያልተመጣጠነ ውድድር ሲፈጥሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በተለይም አንዳንዶቹ ማኅበራት እስከ 30 በመቶ ወለድ እንከፍላለን በማለት የተጋነነ ዋጋ ለብር ሲሰጡ መቆየታቸው በገበያ ላይ የተለያየ የብር ዋጋ እንዲፈጠርና ለገበያ አለመረጋጋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አቶ ገመቹ አስረድተዋል።

እንደ አቶ ገመቹ ገለጻ፤ አዲሱ መመሪያ ትናንሽ ማኅበራትን ከገበያ ያወጣቸዋል የሚል ሥጋት ቢኖርም፣ ይልቁንም ትላልቆቹ ወደ ማይክሮ ፋይናንስነት እንዲያድጉ ሊያበረታታቸው ይችላል።

አሰራሩ ጥቂት ባለሀብቶች በማኅበራቱ ውስጥ ያላቸውን ተጽዕኖ በመቀነስ፣ ተራው ቆጣቢ ዜጋ ያከማቸው ገንዘብ በተሻለ ሁኔታ እንዲጠበቅለትና ዋስትና እንዲያገኝ የሚረዳ መሆኑንም ባለሙያው አክለዋል።

ይህ የብሔራዊ ባንክ የቁጥጥር እርምጃ በሀገሪቱ ያለውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠርና የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማምጣት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ሲሉ የፋይናንስ ባለሙያው አቶ ገመቹ ብርሃኑ አስረድተዋል።

ምንጭ :-ETHIOFM.107.8

ግንቦት 20/2018 ዓ.ም

27/05/2026
 | የተሻሻለው የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ምን አዲስ ነገር አለው??
18/05/2026

| የተሻሻለው የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ምን አዲስ ነገር አለው??

አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የኀብረት ሥራ አዋጅ ማሻሻያ
******
የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ መፅደቁ ለዘርፉ ታሪካዊ እመርታ ነው።

የማሻሻያ አዋጁ ኀብረት ሥራን ከለውጡ ጋር አብሮ የሚራመድ፣ ዘመኑን የዋጀ እና ሀገራዊ የልማት ተልዕኮዎችን የሚያሳካ ዘርፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው።

ኀብረት ሥራን ከባህላዊ የማኅበር አስተሳሰብ ወደ ዘመናዊ የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ተቋምነት የሚያሸጋግር አዲስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው።

ማህበራቱ ከግሉ ዘርፍ ጋር በኢንቨስትመንት እንዲሰሩ፣ አደረጃጀታቸው እንዲጠናከር፣ በተማረ የሰው ኃይል እንዲመሩ እና የኦዲት ተደራሽነት እንዲያድግ የሚያስችል ነው።

በተለይም ማህበራት ከአባላት ውጭ ሼር እንዲሸጡ መፍቀዱ በዘርፉ ታሪካዊ ለውጥ ነው። ይህም ማህበራት ካፒታል ለማፍራት፣ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እና ተወዳዳሪ ቢዝነስ ለመገንባት አዲስ ዕድል ይፈጥራል።

አዲሱ አዋጅ ማህበራት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎች ከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሰፊ ዕድል ይፈጥሯል።

ይህም ማኅበራቱ ያጋጥማቸው የነበረው የስራ ቦታ ገደብ በማንሳት በነፃነትና በሰፊው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ነው።

እንዲሁም አዋጁ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች በራሳቸው እንዲደራጁ ከመፍቀዱ ባለፈ፣ በሌሎች ማህበራት ውስጥ በአመራር ደረጃ የተወሰነ ድርሻ እንዲኖራቸው መደንገጉ የተሳትፎ ፍትሕን የሚያጠናክር ነው።

ከዚህ በፊት በሕግ በግልጽ ያልተደነገጉ የኢንስፔክሽንና የሕግ ማስከበር ሥርዓቶችም በአዲሱ አዋጅ ተካተዋል።

በአጠቃላይ የተሻሻለው አዋጅ፦
🔹 የማህበራትን አደረጃጀትና አመራር ያጠናክራል
🔹 የፋይናንስ ተደራሽነትን ያሳድጋል
🔹 ከግሉ ዘርፍ ጋር የኢንቨስትመንት ትስስር ይፈጥራል
🔹የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ፍትሀዊ ተሳትፎ ያጠናክራል
🔹 የኦዲትና የቁጥጥር ስርዓትን ዘመናዊ ያደርጋል
🔹 ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ያጠናክራል
🔹 የአባላትን መብትና ጥቅም በሕግ ያስከብራል

ቀጣዩ ስራ የማስፈፀሚያ ደንብ ማፀደቅና ከወረቀት ወደ ተግባር በማውረድ የኀብረት ሥራ ማህበራት እውነተኛ አቅም እንዲገለጥ ማድረግ ነው።

ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ = በመርህ የሚመራ ኀብረት ሥራ = ጠንካራ ማኅበራዊ ኢኮኖሚ!

 | የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ==============================6ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ...
14/05/2026

| የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅ ፀደቀ
==============================
6ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኅብረት ሥራ ማህበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሰለሞን ላሌ ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን የተሻሻሉ ጉዳዮችን እና በርካታ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት መሆኑን በዝርዝር አቅርበዋል።

ረቂቅ አዋጁ በተበታታነ ሁኔታ በተለያየ እርከን ተደራጅተው ያሉና ውጤታማ ያልሆኑ ብዙ ቁጥር ያላቸው የኅብረት ሥራ ማህበራት ሰብሰብ ብለው በመደራጀትና ድግግሞሽን በማስቀረት ትርፋማ ለመሆንና የአባላቱን ተጠቃሚነት ከፍ በማድረግ ሌሎችም ወደ አባልነቱ እንዲገቡ የሚያደርግ የአሰራር ሥርዓት የሚዘረጋ መሆኑን ገልጸዋል ።

በማጠቃለያውም ምክር ቤቱ ማሻሻያ አዋጁን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

 | ም/ቤቱ  ነገ በሚያካሂደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባየህብረት ስራ ማህበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል================================== ግንቦት...
13/05/2026

| ም/ቤቱ ነገ በሚያካሂደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባየህብረት ስራ ማህበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል
==================================
ግንቦት 5 ፣ 2018 ዓ.ም፤ 6ኛው ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 21ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ግንቦት 6 ቀን ፣ 2018 ዓ.ም ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ በነገ ስብሰባው የህብረት ስራ ማህበራት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ምንጭ:- ፖርላማ

 / የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት እንዲሁም በጡረታ ፈንዶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ=============================​የኢትዮጵያ ብሔራዊ...
30/03/2026

/ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጠባና ብድር ማኅበራት እንዲሁም በጡረታ ፈንዶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ
=============================
​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ "ጥላ" ተብለው በሚጠሩትና እስካሁን በቂ ቁጥጥር በማይደረግባቸው የፋይናንስ ተቋማት ላይ አዲስ የቁጥጥር መመሪያ ሊያወጣ መሆኑን ገለጸ።

በዚህም መሠረት እስካሁን በኅብረት ሥራ ኮሚሽን ስር ሲመሩ የነበሩት የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱት የጡረታ ፈንዶች በብሔራዊ ባንክ ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር የሚውሉ ይሆናል።

የዚህ እርምጃ ዋና ዓላማ በፋይናንስ ዘርፉ ያለውን ያልተገባ የገበያ ውድድር ለማስቀረት መሆኑን ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

በኢያሱ ዘካሪያስ

ዝርዝሩን ያንብቡ

https://capitalethiopia.com/2026/03/29/nbe-moves-to-regulate-saccos-pension-funds/

11/03/2026

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Sacco posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Sacco:

Share