Ethiopian economy analysis

Ethiopian economy analysis This page works on about Ethiopian economy !!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) ዋና ተልዕኮ የዋጋ መረጋጋትን፣ የፋይናንስ ተቋማትን ደህንነትና ጤናማነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ በዋናነት የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን፣ የውጭ ምንዛሬ ደንቦችን እ...
04/02/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) ዋና ተልዕኮ የዋጋ መረጋጋትን፣ የፋይናንስ ተቋማትን ደህንነትና ጤናማነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ በዋናነት የገንዘብ ፖሊሲ ማሻሻያዎችን፣ የውጭ ምንዛሬ ደንቦችን እና አዳዲስ የባንክ መመሪያዎችን ያስተላልፋል። የቅርብ ጊዜ መረጃዎች የጉምሩክ አመላካች ዋጋዎችን መጠቀም እና የፖሊሲ ለውጦችን ያካትታሉ።

02/02/2026
02/02/2026

ቤተሰብ ይሁኑ፣ ይሳተፉ፣ ይሸለሙ!
የዛሬው ጥያቄ
***********
“የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል ከደንበኞች በስልክ ጥሪ ከሚቀበልባቸው አጭር የስልክ ቁጥሮች መካከል ሶስቱን ይጥቀሱ።”
የባንካችንን የፌስቡክ ገፅ https://www.facebook.com/combanketh በመቀላቀል አሁኑ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ!
ማሳሰቢያ፡
-------------

 በውስጥ መስመር አጭር መልስ ብቻ ይመልሱ፤
 አሸናፊ ከሆኑ በውስጥ መስመር ብቻ መልዕክት ይደርስዎታል እንጂ በስልክ ለሚመጣ ጥያቄ መልስ አይስጡ፤
 የተስተካከሉ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፤
 ቀድመው የመለሱ ስምንት ተሳታፊዎች ይሸለማሉ፤
 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፤
 ሽልማት የሚሰጠው በሲቢኢ ብር ስለሆነ የሲቢኢ ብር ፕላስ ደንበኛ ካልሆኑ መተግበሪያውን አውርደው በራስዎ በመመዝገብ አሊያም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ወይም የሲቢኢ ብር ወኪል በመሄድ ደንበኛ ይሁኑ።

**********
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ለማግኘት፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787


********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#እንኳንደስአላችሁ #ኢትዮጵያንግድባንክ #አገልግሎት #ዕድልእጣ #ኢትዮጵያ

02/02/2026
የፋይዳ መታወቂያን በ"PDF" አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያት…የፋይዳ መታወቂያን በ"PDF" አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት ተቋርጧል አለ የብሔራዊ መታወቂያ ፕ...
02/02/2026

የፋይዳ መታወቂያን በ"PDF" አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያት…

የፋይዳ መታወቂያን በ"PDF" አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት ተቋርጧል አለ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም፡፡

የፋይዳ መታወቂያን በ"PDF" አውርዶ የመያዝ አማራጭ በጊዜያዊነት የተቋረጠበት ምክንያትም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. በየአካባቢው የሚገኙ የኢንተርኔት እና ሕትመት ቤቶች ጥራት በሌላቸው ካርዶች እያተሙ በመሆኑ፣

2. የአንድን ግለሰብ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በፎቶሾፕ እያስመሰሉ በመስራት የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍሎችን እያጭበረበሩ ያሉ አታሚዎች በስፋት መታየታቸው፣

3. ከከተማ ራቅ ብለው የሚኖሩና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ዜጎች ትክክለኛ ባልሆነ የካርድ ሕትመት እየታለሉ ፤ ገንዘብና ጊዜያቸውን ከመጭበርበራቸው ባሻገር የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንዳይችሉ እያደረገ በመሆኑ የሚሉት ናቸው፡፡

ስለሆነም ዜጎች የኢ-ፋይዳ አማራጭ ሲፈልጉ የ"Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ላይ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አመልክቷል፡፡

ኤፍ ኤም ሲን ጠቅሶ አማራ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

02/09/2022
የአለማችንን ኢኮኖሚ የተቆጣጠሩት ድርጅቶች እና አመታዊ ገቢቸው ሲታይ በሚገርም ሁኔታ 85% የሚሆኑት አገሮች አመታዊ ገቢቸው ከነዚህ ድርጅቶች እጅግ ያነሰ ነው።  ይህ ማለት አንድ አገር ከአ...
07/10/2021

የአለማችንን ኢኮኖሚ የተቆጣጠሩት ድርጅቶች እና አመታዊ ገቢቸው ሲታይ በሚገርም ሁኔታ 85% የሚሆኑት አገሮች አመታዊ ገቢቸው ከነዚህ ድርጅቶች እጅግ ያነሰ ነው። ይህ ማለት አንድ አገር ከአንድ የ አሜሪካን ኦሪጅን ድርጅት አመታዊ ገቢ በታች ያገኛል ።

The beauty of tiss abay Ethiopia 🇪🇹
26/09/2021

The beauty of tiss abay Ethiopia 🇪🇹

03/09/2021

በብር የምንዛሪ ተመን ማሽቆልቆል ሳቢያ የዕዳ መጠኑ በ221.5 ቢሊዮን ብር ጨምሯል

መንግሥት ከአገር ውስጥና ከውጭ አበዳሪ ምንጮቹ ላለፉት ዓመታት የተበደረው ውዝፍ የዕዳ መጠን 2.4 ትሪሊዮን ብር ደረሰ።

የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ውዝፍ ዕዳ እ.ኤ.አ. እስከ ጁን 30 ቀን 2021 ድረስ 2.4 ትሪሊዮን ብር ሆኖ መመዝገቡን ይፋ ያደረገው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ያወጣው የዕዳ መግለጫ ሰነድ ነው።

ብሔራዊ ባንክ ላለፈው አንድ ዓመት ባደረገው የብር ምንዛሪ ተመን ለውጥ ምክንያት የብር የመግዛት አቅም በከፍተኛ ደረጃ በመውረዱ፣ አጠቃላይ የአገሪቱ ውዝፍ ዕዳ በ221.5 ቢሊዮን ብር እንዲያሻቅብ ምክንያት እንደሆነም ሰነዱ ያመለክታል።

በዚህም ሳቢያ የኑሮ ውድነቱ ተባብሷል የ ብራችን የመግዛት አቅም እያነሰ በሄደ ቁጥር ዕቃዎች ከውጭ ማስገባት እጅጉን ከባድ ያደርገዋል ለምሣሌ ከዚህ በፊት 300,000 ብር ሲሸጡ የነበሩት ቪትዝ መኪናዎች 700-800ሺህ ብር እየተሸጡ ነዉ።

ጤና ይስጥልኝ ጓዶች የዛሬውን የ ቢሊየነር ባለቤት አማዞን የተሰኘውን ድርጅት አጀማመር በትንሹ እንመለከታለን።      * የ ዚህ አንጋፈ ድርጅት መስራች፡ Jeff Bezos ይባላል       ...
16/08/2021

ጤና ይስጥልኝ ጓዶች የዛሬውን የ ቢሊየነር ባለቤት አማዞን የተሰኘውን ድርጅት አጀማመር በትንሹ እንመለከታለን።
* የ ዚህ አንጋፈ ድርጅት መስራች፡ Jeff Bezos ይባላል
* በ 5 ጁላይ 1994, Bellevue, ዋሽንግተን, ዩናይትድ ስቴትስ እጅግ በጣም ትንሽ በሆነ መዋቅር ተመሰረተ
* በ አሁኑ ሰአት በርካታ ሀገራት እና ከተማዎች ላይ ቁጥራቸው የበዛ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቶች፡ ስያትል, ዋሽንግተን, ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ይገኛሉ
* ከ ሚቀርባቸው products and services መካከል Audible፣ Zappos፣ Whole Foods Market፣ AbeBooks፣ Amazon.ae፣ Amazon Fresh ጥቂቶች ናቸው ።
ዛሬ እኛ መገንዘብ ያለብን ነገር ቢኖር የምንም ነገር መጀመሪያ ትንሽ ሀሳብ መሆኑን ነው።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian economy analysis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share