28/03/2026
መንግሥት መሠረታዊ ካልሆኑ ሥራዎች ውጪ ያሉ ሠራተኞች የዓመት ዕረፍት እንዲወጡ መመሪያ አስተላለፈ
በሀገሪቱ ያጋጠመውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረትና በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የሚታየውን ጫና ለመቀነስ፣ የመንግሥት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች መሠረታዊ ተግባራት ላይ ያልተሰማሩ ሠራተኞቻቸውን የዓመት ዕረፍት እንዲያስወጡ መመሪያ መሰጠቱ ታወቀ።
በዚህ ሳምንት የተላለፈው ይኸው መመሪያ ሁሉንም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ያሉ ተቋማት መመሪያውን በተግባር ላይ ማዋል የጀመሩ ሲሆን፣ "ቁልፍ" ተግባራት ላይ የተሰማሩ ሠራተኞች ብቻ በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙና ቀሪዎቹ ግን የዓመት ዕረፍታቸውን እንዲጠቀሙ በውስጥ ማስታወቂያ አሳስበዋል። በሥራ ገበታቸው ላይ የሚገኙ ቁልፍ ሠራተኞችም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን እንዲጠቀሙ ተነግሯቸዋል።
በኢራን፣ በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ያለው ቀጣናዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ይታወቃል። በመሆኑም በሀገሪቱ ያለውን ውስን የነዳጅ ክምችት በአግባቡ ለመጠቀምና እንደ ቢሾፍቱ አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ላሉ በወር ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ለሚፈልጉ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ ለመስጠት መንግሥት ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
👇👇👇
🔗 t.me/times_mereja_ethiopia
🔗 t.me/times_mereja_ethiopia